Search

ከ100 በላይ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ጀምረዋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ማክሰኞ ሰኔ 30, 2018 121

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በኢትዮጵያ 100 በላይ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶች በይፋ ሥራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞና የቴክኖሎጂ ሽግግር አስመልክተው በሰጡት ሰፊ ማብራሪያ፣ በሀገራችን 5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶችን በኮደርስ ሥልጠና ላይ በመመዝገብ በዚህም ትልቅ ስኬት መመዝገቡን ገልጸዋል።

የቴክኖሎጂ ልማቱ በኢኮኖሚውና በማኅበራዊ ዘርፉ ላይ እያመጣ ያለውን ዘርፈ-ብዙ ለውጥ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በአሁኑ ወቅት የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ እንደሚገኝና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዩኒቨርሲቲ መዋቅርም በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን አስረድተዋል።

አክለውም በተለይም በስታርት አፖች (አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች) በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በገቢ አሰባሰብ እንዲሁም በአጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ላይ ቴክኖሎጂ ከፍተኛና ስትራቴጂካዊ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ በአጽንኦት ገልጸዋል።

በአድማሱ አራጋው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: