Search

ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት ሀብት መጠበቅ ሳይሆን ገቢ ማመንጨት መጀመር አለባቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ማክሰኞ ሰኔ 30, 2018 166

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት ሀብት መጠበቅ ሳይሆን ገቢ ማመንጨት መጀመር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የዘንድሮ በጀት በተቻለ መጠን ወጪ ቆጣቢ መሆን እንዳለበት አንስተው፣ "አደግን ሲባል በልጽገን የጨረስን መምሰል የለበትም፤ ገና ነን ብዙ ጣጣ አለብን" ብለዋል።

ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት ሀብት መጠበቅ ሳይሆን ገቢ ማመንጨት መጀመር አለባቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ፣ ለዚህም የአዲስ አበባን የገቢ አቅም ለአብነት አንስተዋል።

በዚሁም አዲስ አበባ ከለውጡ በፊት የነበረው ገቢ በጣም ዝቅተኛ እንደነበርና በዚህ ዓመት ግን 335 እስከ 340 ቢሊዮን ገቢ ማስገባቱን ገልጸዋል።

ይህም ሪፎርሙ ሲመጣ የኢትዮጵያ መንግሥትም ጭምር የማያስገባ ገቢ መሆኑን ገልጸው፣ በሁሉም ክልሎች ገቢ እንዲሻሻልና በዚያ ልክ ልማት እንዲመጣ ጥረት መደረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

አንድ ሥራ ትጋት፣ ድካምና ዲስፕሊን ከሌለ አይከናወንም፤ እያንዳንዱ ሃብት በዚያው ልክ እንዲመራ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

በግል ዘርፍ የሚሰማሩ ኩባንያዎችም እንደ ነጋዴ ሳይሆን እንደ ገንቢ ራሳቸውን ማየት እንዳለባቸው አጽንዖት ሰጥተው፣ ጥራት ያለውንና ለልጆቻችን የሚሸጋገረውን ነገር መሥራት ላይ ማተኮር አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል።

ወደ ክልል የሚላከው በጀት ለታለመለት ዓላማ መዋሉን መቆጣጠር ማረጋገጥ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የሚቀጥለው ዓመት ከፍተኛ ሥራ የሚፈልግ ዓመት መሆኑን አንስተው፣ እስካሁን ከነበረን ፈተናና ካገኘነው ድል በላይ የሚጠብቀን ዓመት ነው ሲሉም አጽንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።

በአድማሱ አራጋው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: