የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከፌደራልና ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን፣ “የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም” የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀምን እየገመገመ ይገኛል።
በገጠር አካባቢዎች የመንገድና የትራንስፖርት መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት፣ የግብርና ምርታማነትንና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተነደፈው ይህ ፕሮግራም፤ በአሁኑ ወቅት በ126 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው፤ እስካሁን በድምሩ 1 ሺህ 123 የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል። በእነዚህ ዘርፈ-ብዙ ሥራዎችም ከ3.4 ሚሊዮን በላይ የገጠሩ ማኅበረሰብ አባላት ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።
ይህ ተደራሽነት አርሶ አደሩ ምርቱን ያለ እንግልት ወደ ገበያ እንዲያቀርብ ከመደገፉም በላይ፤ እንደ ጤናና ትምህርት ያሉ ወሳኝ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በአቅራቢያው እንዲያገኝ ሰፊ ዕድል ፈጥሯል።
በተጨማሪም የመንገድ መሠረተ ልማት ባለመኖሩ ምክንያት ከምርት ስብሰባ በኋላ የሚከሰተውን የሰብል ብክነት በከፍተኛ ደረጃ የሚገታው ይህ ፕሮጀክት፤ ለአካባቢው ማኅበረሰብ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ተገልጿል።
በዓለም ይልፉ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: