Search

ከተመጽዋችነት ወደ ሉዓላዊነት

ሰኞ ነሐሴ 18, 2018 40

ሰፊ ለም መሬት፣ የከርሰ ምድር እና የገጸ ምድር ውኃ፣ እንዲሁም አምራች ወጣት ኃይል ያላት ኢትዮጵያ በተመጽዋችነት ስሟ መነሣቱ፣ የዜጎቿን የምግብ ፍላጎት ለመሙላት የምግብ ዕርዳታ መጠበቋ ሀገራዊ ክብርን የሚነካ ነው።

እውነተኛ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ነጻነት የሚረጋገጠው በቅድሚያ የምግብ ሉዓላዊነት ሲረጋገጥ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ያነሣሉ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምግብ ሉዓላዊነት ራዕይ፣ኢትዮጵያ በምግብ አቅርቦት በራሷ እግር መቆም አለባት፤ የዕርዳታ እጅ መዘርጋት መቆም አለበትበሚለው አስተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ነው።

ይህንን ታሳቢ በማድረግም የቀደመውን የተመጽዋችነት ምዕራፍ ዘግቶ ከልመና ወደ ኩራት እና ሉዓላዊነት ለማሻገር በስፋት እየተሠራ ነው፤ ስኬቶችም ተመዝግበዋል።

ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ እና በምግብ ራሷን ለመቻል ባለፉት ጥቂት ዓመታት ትኩረት ሰጥታ እየተገበረቻቸው ባሉ ፕሮጀክቶችም ስኬቶች ተመዝግበዋል።

ለአብነትም፣ በመስኖ የሚለማ የስንዴ መሬት ከጥቂት ዓመታት በፊት ከነበረበት በሺዎች ከሚቆጠር ሔክታር በአሁኑ ወቅት 4 ሚሊዮን ሔክታር በላይ ማልማት ተጀምሯል። አጠቃላይ የስንዴ ምርትም 330 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማደግ ችሏል።

"የማይቻል ነገር የለም" በሚል እምነት የተጀመረው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ኢትዮጵያ ከውጭ ስንዴ ማስገባቷን አቁማ በራሷ አቅም አምርታ ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደምትችል በተግባር ያሳየ ታላቅ ማረጋገጫ ሆኗል።

በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ፣ የምግብ ሉዓላዊነት ማለት የእህል ምርት ብቻ ሳይሆን የወተት፣ የዶሮ፣ የማር እና የእንስሳት ተዋጽኦን ማሳደግ በመሆኑ፣ በወተት፣ በእንቁላል እና ዶሮ፣ በሥጋ እንዲሁም በክላስተር የንብ ማር ምርት ላይም ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።

ጅምሮቹ የኢትዮጵያን የአፍሪካ የምግብ ቅርጫት የመሆን ራዕይ ተጨባጭነት ያመላክታሉ።

ሀገራችን፣ በምግብ ራሷን ከመቻል አልፋ የጎረቤት እና የሌሎች አፍሪካ ሀገራትን የምግብ ፍላጎት የማሟላት እና ለአህጉሩ የምግብ ዋስትና ትልቅ አስተዋጽኦ የማበርከት አቅም እንዳላትም ጠንካራ ጠቋሚዎች ናቸው።

በዓይናለም ሃድራ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: