Search

የቀጣናውን ሰላም ለማረጋገጥ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ትሰራለች፡- አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ

ዓርብ ሐምሌ 03, 2018 159

የቀጣናውን ሰላም ለማረጋገጥ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደምትሰራ  በኢትዮጵያ የአሜሪካ  አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ገለጹ።

አምባሳደር ማሲንጋ የሕዝብ በአዲስ አበባ እተካሄደ ባለው ዓለም አቀፉ የፓርላማ የመረጃና ደኅንነት ፎረም ባደረጉት ንግግር የምስራቅ አፍሪካን ቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋት አስተማማኝ ለማድረግ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በደህንነትና በትብብር መስኮች ይበልጥ በቅርበት ለመስራት ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

አምባሳደሩ በተለይም እንደ ሽብርተኝነት፣ ድንበር ተሻጋሪ የደኅንነት ሥጋቶች እና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን የመሰሉ ውስብስብ ቀጣናዊ ችግሮችን በጋራ ለመከላከል የመረጃ ልውውጥና የተቋማት የጋራ ትብብር ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።

የደኅንነት ተቋማት መጠናከር ለኢትዮጵያና ለቀጣናው ዘላቂ አስተማማኝ ሰላምና ደኅንነት መረጋገጥ ዋነኛ መሠረት መሆኑን አምባሳደሩ መጠቆማቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል።

አሜሪካ በቴክኖሎጂና በደኅንነት ዘርፎች ጭምር ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ አጋርነት ይበልጥ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ አጠናክራ ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላትም አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በንግግራቸው ይፋ አድርገዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: