Search

የመንግሥት ሆስፒታሎች የትናንትናው ሁኔታቸው እየተቀየረ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ቅዳሜ ሐምሌ 04, 2018 55

በአዲስ አበባ አስተዳደር ስር የሚገኙ የመንግሥት ሆስፒታሎች የትናንትናው ሁኔታቸው እየተቀየረ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ለዘመናት ተዘንግተው በእርጅና የተጎሳቆለውና የቆሸሸው ገፅታቸው በአዳዲስ ዘመናዊ ህንፃዎች እየተተካ፣ ኋላቀር  የነበሩት የህክምና መሳሪያዎች ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን በሚጠቀሙ መሳሪያዎች እየተቀየሩ የታካሚውን ብቻ ሳይሆን የሀኪሞቻችንን ሥራም እያቃለሉ ነው ብለዋል።

በተለይም አንዳንዶቹ ጠረናቸው ተቀይሯል፤ ወደ ቅጥር ጊቢያቸው ሲገባ ንፁህ የፈውስ ስሜት ይፈጥራሉ ሲሉም አክለዋል።

ለዚህም ዘውዲቱ መታሰቢያ፣ ሚኒልክ  እና ትናንት የመረቅነው ራስ ደስታ ህያው ማሳያዎች መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ አመልክተዋል።

ይህ ሁኔታ በሁሉም ሆስፒታሎች እንዲተገበር ጠንክረው እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: