የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያከናወነው ባለው የማያቋርጥ የኔትዎርክ ማስፋፊያ ሥራ ወደ ሞሪሽየስ አዲስ የበረራ አገልግሎት ዛሬ በይፋ ጀምሯል።
አየር መንገዱ በሳምንት ሦስት ቀናት ወደ ሞሪሽየስ የሚበር ይሆናል።
ወደ ሞሪሽየስ ቀጥተኛ በረራ መጀመሩ ጎብኚዎች ወደ ደሴቷ ለመጓዝ የሚፈጅባቸውን ጊዜ በእጅጉ እንደሚቀንሰው ተገልጿል።
አዲሱ በረራ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስርንም እንደሚያጠናክር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።
በተጨማሪም በረራው የሞሪሽየስን የቱሪዝም ሀብት ለዓለም ለማስተዋወቅ እንደሚያግዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የሞሪሽየስ አምባሳደር ኢንድራርጄት ባቦ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ለማስተሳሰር እና ለማስተዋወቅ እያከናወነው ያለውን ሥራ አድንቀዋል።
የበረራው መጀመር የቱሪስት መዳረሻ የሆነችውን ሀገራቸውን ለማስተዋወቅና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፣ የበረራው መጀመር የሁለቱ ሀገራት ትስስር እየተጠናከረ የመምጣቱ ማሳያ ነው ብለዋል።
በአባዲ ወይናይ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: