Search

“የሕዝቡ ጥያቄ የተመለሰው ሕዝባዊ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን ትክክለኛና ተገቢ ስለሆነ ነው”፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

እሑድ ሐምሌ 05, 2018 31
 
የደብረ ማርቆስ ከተማ የአውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት ዳግም መጀመሩን ተከትሎ፣ ዘመናዊው የንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ በይፋ ተመርቋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ ከተማዋ ከ60 ዓመታት በፊት የአውሮፕላን ማረፊያ የነበራት ቢሆንም፣ ለረጅም ዘመናት አገልግሎት ከሰጠ በኋላ እንዲቀር መደረጉን አስታውሰዋል።
 

 
 
የሕዝቡ የዘመናት ጥያቄ በለውጡ መንግሥት መመለሱን የገለጹት አቶ ተመስገን፣ ጥያቄው የተመለሰው ሕዝባዊ ብቻ ሳይሆን ትክክለኛና ተገቢ በመሆኑ ነው ብለዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም፣ የአውሮፕላን ትራንስፖርት አገልግሎቱ መጀመር የአካባቢውን ቱሪዝምና ንግድ የበለጠ እንደሚያሳልጥ ተናግረዋል።
የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያን በመሠረተ ልማት ማስተሳሰርና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን መገንባት ዋና ተልዕኮው መሆኑን በመግለጽ፣ ይህንን የልማት ሥራ በሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: