ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቤኒን ፕሬዚዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒን ተቀብለው በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ያደረጉት ውይይት የኢትዮጵያን እና የቤኒንን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እና በጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሠረተ የላቀ ትብብር ለማድረግ በሚያስችሉ ዕድሎች ዙሪያ ያተኮረ ነው። ውይይቱ ፍሬያማ እንደነበርም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ከቤኒን ጋር ያላትን ጥልቅ አጋርነት እና ዘላቂ ወዳጅነት ይበልጥ ለማሳደግ ጽኑ ፍላጎት እና የጋራ ቁርጠኝነት መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: