Search

ከጥፋት እና ከጥላቻ አዙሪት ይልቅ የሰከነ ውይይትን እና ምክክርን የመረጠችው ኢትዮጵያ

ሰኞ ሐምሌ 06, 2018 160

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ካልተገባ ፖለቲካዊ ውጥረት፣ ከጥላቻ ንግግሮች እና ከጠብ አውዳሚ መንገድ ይልቅ የሰከነ ውይይት እና ሁሉን አቀፍ ምክክርን ብቸኛ እና አስተማማኝ የነገ መዳረሻዋ አድርጋ መርጣለች።

በውስጥም ሆነ በውጭ የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች እና የታሪክ አጋጣሚዎች ለመፍታት ወደ ግጭት እና አለመግባባት ከመሄድ ይልቅ በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገርን፣ መደማመጥን እና መመካከርን ቀዳሚ ስልቷ አድርጋ በፅናት እየተገበረችው ትገኛለች።

ይህ ኢትዮጵያ የያዘችው የሰከነ ውይይት መርሕ በጥላቻ ላይ ለሚሰሩ አጀንዳዎች እንዲሁም የሀገርን ህልውና ለመፈታተን ለሚሞክሩ አካላት ትልቅ ምላሽ የሚሰጥ ነው።

ጦርነት፣ ጠብ እና ጥላቻ ሀገርን ወደኋላ ከመጎተት እና ሕዝብን ከማፈናቀል ባለፈ የሚያተርፉት ምንም ነገር የለም።

በመሆኑም ይህንን እውነት በሚገባ በመገንዘብ ልዩነቶችን በኃይል ሳይሆን በመቻቻል፣ በታማኝነት እና በምክክር መፍታት እንደሚቻል በተግባር እያሳየች ያለችው ሀገራችን የጋራ መግባባትን በመፍጠር የብሔራዊ አንድነቷን መሰረት እያጠናከረች ትገኛለች።

ሀገራዊ ምክክሩ ሀገርን በጥላቻ ከሚመጣ ጥፋት የሚታደጉ የሰላምን ዋጋ ከፍ የሚያደርጉ እና ለዘላቂ ብሔራዊ መግባባት መንገድ የሚጠርግ ነው።

ምክክርን፣ መደማመጥን እና የሰከነ ውይይትን ምርጫዋ ያደረገችው ኢትዮጵያ የነገውን ብሩህ እና ጠንካራ ጉዞዋን በማይናወጥ መሠረት ላይ እየገነባች ትገኛለች።

በሃና ምንዳሁን

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: