Search

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል

ሰኞ ሐምሌ 06, 2018 161

6ኛው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ነገ ሐምሌ 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ በነገው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በጣልያን ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል እንዲሁም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በፈረንሳይ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የተደረጉ የብድር ስምምነቶችን ለማጽደቅ የሚቀርቡ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: