ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ጋር በመሆን በኤ አይ (AI) ዩኒቨርሲቲ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።
“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ በአዲስ አበባ ከተማ 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።
ከንቲባዋ እንደገለጹት፣ ከሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ባለው ጊዜ ውስጥ 4 ሚሊዮን 469 ሺህ 710 ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ የዕቅዱን 75 በመቶ አፈጻጸም ማሳካት ተችሏል።
አያይዘውም ችግኝ መትከል ብቻውን ለታለመው ግብ እንደማያደርስ የገለጹት ከንቲባ አዳነች፣ የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: