Search

በምክክር የምትፀና ኢትዮጵያ

ረቡዕ ሐምሌ 08, 2018 117

የኢትዮጵያ ዘላቂ ሕልውና፣ ሰላም እና ዕድገት የሚረጋገጠው በኃይል ሳይሆን በሕዝቦቿ መካከል በሚደረግ እውነተኛ፣ ግልጽ እና አካታች ምክክር ነው።

ምክክር የልዩነቶች መፍቻ፣ የጋራ እሴቶች መገንቢያ እና የጽኑ ሀገረ-መንግሥት መሠረት ነው።

ምክክር ማለት ልዩነቶችን ማጥፋት ሳይሆን ልዩነቶችን አክብሮ እና አስተናግዶ በጋራ ጉዳዮች ላይ መስማማት ነው።

በውይይት እና በንግግር የሚፈታ ችግር በሕዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላምን፣ መከባበርን እና ወንድማማችነትን ያጠናክራል።

በምክክር ሂደት ውስጥ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች ሐሳባቸው፣ ስጋታቸው እና ተስፋቸው ሲካተት ሀገራዊ ውሳኔዎች የጥቂቶች ሳይሆኑ የሙሉው ሕዝብ ይሆናሉ። ይህም በዜጎች ዘንድ የሀገር ባለቤትነት ስሜትን ይፈጥራል።

በሰፊ ሀገራዊ ውይይት የተገነባ የፖለቲካ እና የሕግ ሥርዓትም  ከማንኛውም አካል ፍላጎት በላይ ሆኖ ይጠናከራል። መተማመን በተፈጠረበት ማኅበረሰብ ውስጥ ተቋማት ገለልተኛ እና ጠንካራ በመሆን የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ይችላሉ።

በምክክር ማመንን ማሳደግ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር በሳል የፖለቲካ ባህል ይፈጥራል። የጠብመንጃ አፈሙዝ እና የፀብ መንገድን በማስወገድ፣ በምክክር ችግሮችን የመፍታት ልምድን ያጎለብታል።

በምክክር የምትፀና ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጎቿ ድምፅ የሚሰማበት፣ ፍላጎታቸው የሚከበርበት እና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው በጋራ የሚወሰንበት ጥንካሬ ይኖራታል።

በበረከት ሽመልስ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: