3ኛው የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ጠቅላላ ጉባዔ በአዳማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ የሕዝብን የጋራ መረዳጃ እሴት ወደ ዘመናዊ ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት በመቀየር፣ ጊዜያዊ ድጋፍን ብቻ ሳይሆን ለማኅበራዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ በመስጠት ረገድ ሰፊ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ በጉባዔው ላይ ተገልጿል።
የቡሳ ጎኖፋ መሥሪያ ቤት በቆላማ አካባቢዎች ለሚኖረው ኅብረተሰብ የውኃ ችግርን ለማቃለል ከ600 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ 30 የውኃ ቦቴ መኪናዎችን አስረክቧል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ፣ ለማኅበረሰቡ የቀረቡትን እነዚህን የውኃ ቦቴ መኪናዎች በይፋ አስረክበዋል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሕዝብን ተሳትፎ እና የመንግሥትን ቅንጅት በማጠናከር፣ በቡሳ ጎኖፋ በኩል እንደ ውኃ እጥረት፣ እንዲሁም የተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ባሉ ማኅበራዊ ችግሮች ላይ ፈጣን እና ዘላቂ ምላሽ ለመስጠት ቀጣይነት ያለው ሥራ እያከናወነ ይገኛል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: