Search

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን 266.9 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘ

ዓርብ ሐምሌ 10, 2018 147

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች 2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸማቸውን በሀዋሳ ከተማ በመገምገም ላይ የሚገኙ ይገኛሉ፡፡ 

2018 በጀት ዓመት 266.9 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከውጭ ንግድ ገቢ መገኘቱ መግምገማው ወቅት ተነግሯል።

ገቢው የተገኘው ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ባለሀብቶች እየተመረቱ ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች መሆኑ ተጠቅሷል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (/) ዘንድሮ የተገኘው ይህ የውጭ ምንዛሬ ገቢ በተቋሙ ታሪክ የተመዘገበ ከፍተኛው አፈጻጸም መሆኑን ገልጸዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይህ ውጤት ኮርፖሬሽኑ ካወጣው የአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ጋር ሲነጻጸር የተቀመጡ ግቦችን ቀድሞ የማሳካት አቅም እንዳለው የሚያሳይ አበረታች ምዕራፍ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለዚህ ታሪካዊ ስኬት ዋነኛው ምክንያት በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ለሚገኙ ባለሀብቶች እና አምራች ኩባንያዎች የሚደረገው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እና የቅርብ ክትትል ተጠናክሮ መቀጠሉ መሆኑ ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: