Search

አዲስ አስመጪዎች እና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሒሳብ ቁጥርን በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አንድ መስኮት አገልግሎት በኩል እንዲያገኙ ተፈቀደ

ዓርብ ሐምሌ 10, 2018 184

 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር፣ አዲስ ፈቃድ ላወጡ አስመጪዎች እና ላኪዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሒሳብ ቁጥር አሰጣጥን የሚያቀል አዲስ የዲጂታል አገልግሎት አስተዋውቋል።

ይህ አገልግሎት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሒሳብ ቁጥሮች በጉምሩክ ኮሚሽን አንድ መስኮት አገልግሎት (Customs Electronic Single Window - eSW) በኩል ያለምንም ውጣ ውረድ እንዲሰጥ በማስቻል፣ አስተዳደራዊ ሂደቶችን የሚቀንስ እና ፈጣን የንግድ አሠራርን የሚደግፍ መለሆኑን ባንኩ ገልጿል።

አዲሱ አገልግሎት የሚመለከተው ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሒሳብ ቁጥር ለሚያወጡ እና አዲስ ፈቃድ ላገኙ አስመጪዎች እና ላኪዎች ብቻ ነው።

ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሒሳብ ቁጥር ያላቸው የንግድ ተቋማት ለሁሉም የገቢ እና የወጪ ንግድ ግብይቶቻቸው ይጠቀሙበት በነበረው ነባር ቁጥር መጠቀም ይችላሉ።

ይህ አሠራር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገቢ እና የወጪ ንግድ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን ለማዘመን፣ የንግድ አሠራርን ምቹ ለማድረግ፣ እንዲሁም የዲጂታል የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጠናከር እያከናወነ ያለው ቀጣይ ጥረት አካል ነው።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: