የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትስሰር ገጽ መልዕክታቸው፣ "ከርዕሰ መስተዳድሯ ጋር አንዳንድ ሥራዎችን በትብብር ለመስራት ፍሬያማ ውይይት አድርገናል" በለዋል።
በቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ፣ በኮሪደር ልማት፣ እንዲሁም በሌሎች የሰው-ተኮር ሥራዎች ዙሪያ እርስ በርስ ልምድ ለመለዋወጥ፣ ትብብራቸውን አጠናክረው በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ጠቅሰዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: