የትግራይ ሕዝብ ጠላቱ የሆነውን ሕገ-ወጡ ህወሓት ቡድን እምቢ ሊል ይገባል ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።
ሕገ-ወጡ የህወሓት ቡድን በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚፈፅመውን አፈና እና ጭቆና የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የተገኙት አቶ ጌታቸው ረዳ ባስተላላፉት መልዕክት፣ ሕገ ወጡ የህወሐት ቡድን ወጣቶችን ወደ ሱዳን መሸጥ ያቁም፤ ያሉ ሲሆን ቡድኑ የትግራይን ሕዝብ ከልማት ወደ ኋላ ያስቀረ ነውም ብለዋል።
ከሀገር ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን የቡድኑን እድሜ ለማሳጠር እንዲሠሩም ጥሪ አቅርበዋል።
ትግራይ በ አጭር ግዜ ወደ ሰላም እንድትመለስም በጋራ መሥራት ይገባል ብለዋል።
ይህ ሰላማዊ ሰልፍ በትግራይ እናቶች ላይ የሚደርሰውን አፈና፣ ድብደባና በደል፣ የሺዎች ተጋሩዎችን መፈናቀል፣ የወጣቱን ሞትና ስደት እንዲሁም የሕዝቡን መከራ ለማስቆም የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
ሰልፉ በሕዝብ ስቃይ ላይ የራሱን ኅልውና ለመገንባት በሚፈልገው “የኋላ ቀር ቡድን” እና በጦርነት ላይ ያለንን ተቃውሞ የምናሰማበት ነው ሲሉም አክለዋል።
በትግራይ ሕዝብ ላይ ሰላም ሊሰፍን እንደሚገባ ድምፃችንን የምናስተጋባበት አጋጣሚ በመሆኑ፣ የሕዝቡ ኅልውና እና ሰላም የሚያሳስበው ሁሉም ወገን ድምፁን እንዲያሰማ ጥሪ ቀርቧል።
ሰልፉ የትግራይ ሕዝብ እየደረሰበት ያለውን መከራ፣ መፈናቀልና ጦርነት በመቃወም፣ ለሰላምና ለኅልውናው በጋራ ድምፅን ለማሰማት የቀረበ ጥሪ መሆኑም ተመላክቷል።
በዳሃብ ያሲን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: