Search

ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

እሑድ ሐምሌ 12, 2018 150

የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛው የሥራ ዘመን፣ 5ኛው ዓመት 11 መደበኛ ጉባኤውን በጨፌ አዳራሽ ማካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው 2018 በጀት ዓመት የሥራ አስፈጻሚ አካል የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እና 2019 . የዕቅድ አቅጣጫዎች፣ እንዲሁም የሕግ ተርጓሚ አካል የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለጨፌው አባላት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

2018 . ተጨማሪ በጀት 84 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም 2019 በጀት ዓመት 704 ቢሊዮን ብር የረቂቅ አዋጅ ለጨፌው ይቀርባል።

በተጨማሪም የዳኞች ሹመት ለጨፌው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በሃይማኖት ከበደ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: