Search

"በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ ለሚል አካል አሁንም የሰላም በሩ ክፍት ነው" - አቶ ሽመልስ አብዲሳ

እሑድ ሐምሌ 12, 2018 133

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሰላም ጥሪውን ተቀብሎ በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ ለሚል አካል የተከፈተው የሰላም በር አይዘጋም ሲሉ ገለጹ።

የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛው የሥራ ዘመን፣ 5ኛው ዓመት 11 መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ ጉባኤ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ 2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እና 2019 . ዕቅድን እያቀረቡ ነው።

የክልሉ መንግሥት ከምንም በላይ ሰላምን ለማረጋገጥ እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን በሪፖርታቸው ገልጸዋል።

መንግሥት ሕዝቡን በሚገድል፣ በሚዘርፍ እና በሚያሸብር ኃይል ላይ ያልተቋረጠ የሕግ የበላይነትን የማስከበር እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

የክልሉ መንግሥት ከፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች ቅንጅት እና ከሕዝቡ ትብብር ጋር በመሆን፣ በርካታ ቁጥር ያላቸውን የጥፋት ኃይሎች ማጥፋት፣ መማረክ እና እጃቸውን እንዲሰጡ ማድረግ መቻሉንም ተናግረዋል።

መንግሥት በአቋራጭ ሥልጣን ለመያዝ ካለው ሕልም ተስፋ መቁረጥ አቅቶት በጫካ ውስጥ የቀረውን ኃይል አድኖ ለሕግ እንደሚያቀርብ አቶ ሽመልስ ገልጸዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: