Search

ውበት፣ ገቢ እና ምግብ በአንድ ላይ ያጣመረው የአቮካዶ ደን በኢትዮጵያ

እሑድ ሐምሌ 12, 2018 134

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) የተጀመረው እና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያለመው ብሔራዊ የአቮካዶ ፕሮግራም በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ 157 ወረዳዎች ላይ በተጠናከረ መልኩ እየተገበረ ይገኛል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለአቮካዶ ምርት ያለውን ምቹ የአየር ንብረት በመጠቀም ወደ ሥራው በስፋት መግባቱን እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመረጡት ወረዳዎች ውስጥ አስሩ ወረዳዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ መሆናቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር አስታውቀዋል።

አቮካዶ የአካባቢን ሥነ-ምህዳር የሚያሻሽል፣ ውበትን የሚሰጥ፣ እንዲሁም አስተማማኝ የምግብ እና የገቢ ምንጭ መሆኑ ተገልጿል።

ዘንድሮ የሚተከሉ የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኞች በብዛት ለምግብነት የሚውሉ ላይ ያተኮሩ ሲሆን፣ ቀድሞ የነበረውን ምርት ይበልጥ ለማሳደግ "የአቮካዶ ደን" የመፍጠር ሥራም እየተሠራ ይገኛል።

ይህ ንቅናቄ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን እንደ ሀገር ደግሞ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና አለው።

በቅርቡም ኢትዮጵያ የአቮካዶ ምርትን ለውጭ ገበያ በማቅረብ በአፍሪካ 2 ደረጃን መያዟ ይታወሳል።

በአስማረ ብርሃኑ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: