Search

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከ595 ሺህ በላይ ለሚሆኑ መዝገቦች እልባት መስጠቱን አስታወቀ

ሰኞ ሐምሌ 13, 2018 144

በኦሮሚያ ክልል በ2018 በጀት ዓመት በሦስቱ የመንግሥት ፍርድ ቤቶች ደረጃ የፍትሕ አገልግሎት ቀልጣፋነትን ለማሻሻል በተደረገው ጥረት በእንቅስቃሴ ላይ ከነበሩ 608 ሺህ 889 መዝገቦች ውስጥ 595 ሺህ 199 መዝገቦች እልባት ማግኘታቸውን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል።

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ገዛሊ አባሲመል የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የወደፊት የዕቅድ አቅጣጫን ለጨፌ ኦሮሚያ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ ውሳኔ ካገኙት አጠቃላይ መዝገቦች መካከል 585 ሺህ 372 የሚሆኑት በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ እልባት ያገኙ ናቸው።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም የፍትሕ ሥርዓቱን እሴትና የሥራ ሥነ-ምግባር በመጣስ የሥነ-ምግባር ግድፈት ፈጽመው መገኘታቸው በተረጋገጠ 318 የፍትሕ ሥርዓቱ አባላት ላይ እንደ ጥፋታቸው ክብደት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፣ የደመወዝ ቅጣት፣ ከደረጃ ዝቅ ማድረግ እና ከሥራ ማሰናበትን ጨምሮ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ጠቁመዋል።

ከዚህ በተያያዥም ፍርድ ቤቱ በፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን ከመሠረቱ ለመፍታትና የፍትሕ አሰጣጡን በቴክኖሎጂ የተደገፈ (E-Court) ለማድረግ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መግባቱን ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ገልጸዋል።

በሃይማኖት ከበደ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: