በታሪክ ውጣ ውረዶች እና በአጋጣሚዎች ከባሕር በር ግንኙነት ተነጥላ የቆየችው ኢትዮጵያ ይህንን ስልታዊ ጥቅም በሰላማዊ እና በሕጋዊ መንገድ ለማስመለስ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ቀጥላለች።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ከጂኦፖለቲካዊ ፍላጎት ባለፈ የነገዋን ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት እና የኢኮኖሚ ዕድገት እውን የሚያደርግ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።
ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛቷ፣ በማደግ ላይ ባለው ኢኮኖሚዋ እና በቀጣናው ባላት ቁልፍ ሚና ከባሕር በር ጋር መገናኘቷ የማይቀር ታሪካዊ ፍላጎት ነው።
በታሪክ ሂደት በተፈጠሩ ተግዳሮቶች ያጣችውን የባሕር በር መዳረሻ በሰላማዊ ዲፕሎማሲ እና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ለመመለስ የሚደረገው ጥረት የኢትዮጵያን ሉዓላዊ የኢኮኖሚ ደህንነት የማረጋገጥ ሰፊ አቅም የያዘ ነው።
የአሁኑ ትውልድ ይህንን ታሪካዊ ክፍተት ለመሙላት በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን፣ የባሕር በር ባለቤት መሆን የሎጂስቲክስ ወጪዎችን በእጅጉ በመቀነስ የውጭ ንግድን እና ኢንቨስትመንትን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይታመናል።
ይህ ስልታዊ እርምጃ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ምርቶች ያለ ገደብ ወደ ዓለም ገበያ እንዲደርሱ እና የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ግዙፍነት እንዲረጋገጥ የሚያስችል ትልቁ ድል ነው።
ከሁሉም በላይ ደግሞ በየጊዜው እየተለዋወጣ ባለው የቀይ ባሕር ቀጣና የደኅንነት ፈተና ውስጥ ኢትዮጵያ ብሔረዊ ደኅንነቷን እና የቀጣናውን ሰላም ሚዛን እንድትጠብቅ ያደርጋታል፡፡
የነገዋ ኢትዮጵያ ተስፋ ከባሕር በር ጋር አብሮ የሚንሰራራ የሰላም እና የልማት ትስስርን የሚያጠናክር እንዲሁም የኢትዮጵያን የዘመናት ናፍቆት በድል የሚቋጭ ነው።
በሃና ምንዳሁን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: