Search

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማስተርካርድ ፋውንዴሽን የአፍሪካ ሽልማት አሸናፊ ሆነ

ማክሰኞ ሐምሌ 14, 2018 114

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማስተርካርድ ፋውንዴሽን የአፍሪካ ከፍተኛ ትምህርት ለለውጥ (AHEFT) የመጀመሪያው ዙር ሽልማት አሸናፊ በመሆን ተመረጠ።

ዩኒቨርሲቲው የተቋማዊ ለውጥን በመምራት እና ለወጣቶች ዕድሎችን በማስፋፋት ዕውቅና ከተሰጣቸው አምስት የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ነው።

ሽልማቱ በምርምር፣ በፈጠራ፣ በሰው ኃይል ልማት እና በማህበረሰብ ተፅዕኖ ላይ የሚያከናውነውን ሥራ ይበልጥ ለማጠናከር የሚረዳ 3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍን ያካትታል።

ይህ ታላቅ ዕውቅና ስትራቴጂክ ዕቅዱን እና ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር ያለውን የረጅም ጊዜ አጋርነት የሚያንፀባርቅ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ይህን ዕድል ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ የሚሆን የምርምር ብቃት፣ ፈጠራ እና ለውጥ አምጪ ትምህርትን ለማጠናከር እንደሚጠቀምበትም ጠቁሟል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: