Search

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፍሪካ ኅብረት አስቸኳይ የጤና ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጋና ገቡ

ማክሰኞ ሐምሌ 14, 2018 66

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፍሪካ ሕብረት አስቸኳይ የጤና ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ መነሻዎች አንዷ በሆነችው አክራ ጋና መግባታቸውን አስታወቁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባጋሩት መረጃ የታዋቂው ፓን-አፍሪካኒስት መሪ ክዋሜ ንክሩማህ ምድር በሆነችው ጋና በሚኖራቸው ቆይታ በአፍሪካ የጤና ሥርዓት ዙሪያ እንደሚመክሩ ገልጸዋል።

በጉባኤው በተለይም የአህጉሪቱን የጤና ሥርዓት ለማሻሻል እንዲሁም ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ ስልታዊ እርምጃዎችን ለመቀየስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚያደርጉም አመልክተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በአክራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና በሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ ለተደረገላቸው አቀባበልም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: