Search

ምድራችንን እንታደግ፡ ታሪክን የሚቀይረው የአረንጓዴ ዐሻራ

ሓሙስ ሐምሌ 16, 2018 166

የሰው ልጅ የቴክኖሎጂ አቅም በጠፈር ላይ አዳዲስ ዓለማትን እስከ መፈለግ በደረሰበት በዚህ ዘመን፣ የቆምንባት ምድራችን ግን በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተራቆተች ትገኛለች።

የቀደሙት ታላላቅ ሥልጣኔዎች ውድቀት እንደሚያስረዳው የመሬት መራቆት እና የውኃ መከፋፈል የምግብ እጥረትን እና የሕዝቦች ስደትን በማስከተል የታሪክ አቅጣጫን ቀይረዋል።

ይህንን ዓለም አቀፋዊ አደጋ ለመመከት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ... 1994 የበረሃማነት መከላከል ስምምነትን (UNCCD) ማጽደቁ አይዘነጋም።

የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ 2026 .የወደፊት ህይወታችንን ለመጠበቅ መሬታችንን መጠበቅ ይኖርብናል:: በየትኛውም ስፍራ የሚገኙ የጋራ ሥነ-ምህዳሮቻችን እና የግጦሽ መሬቶቻችን ለመጪው ትውልድ በልምላሜ እንዲቀጥሉ በጋራ እንስራሲሉ ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በረሃማነት የደረቅ እና ከፊል ደረቅ አካባቢዎች ለምነት መክሰም ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የመሬት ያለ እረፍት መታረስ፣ የእንስሳት አብዝቶ መሰማራትና የዛፎች መቆረጥ ለም አፈሩ በነፋስና በጎርፍ እንዲጠረግ በማድረግ አካባቢውን ወደ መካን አቧራ የሚቀይር አደጋ ነው።

በአሁኑ ወቅት 2 ቢሊዮን በላይ የሚሆነው የዓለም ሕዝብ በተለይም 90 በመቶ ያህሉ በማደግ ላይ ባሉ አገራት የሚኖሩ ዜጎች የዚህ ቀውስ ቀጥተኛ ገፈት ቀማሾች ናቸው።

ከዚህም በላይ የቁም እንስሳት መዋያና የግጦሽ መሬቶች አጋማሽ አካል ተመናምነዋል፤ ይህም በቀጣዩ አስር ዓመት ውስጥ 50 ሚሊዮን ሰዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው ሊያፈናቅል የሚችል የህልውና ስጋት ደቅኗል።

ኢትዮጵያ ይህንን ዓለም አቀፋዊ የሥነ-ህይወት ውድመት ለመቀልበስ የያዘችው መንገድ ግን ባህላዊ የተናጠል እርምጃዎችን በመሻገር የላቀ ዲፕሎማሲያዊና ስትራቴጂያዊ ግንባር ቀደምትነትን የተላበሰ ነው።

2011 .. ጀምሮ ይፋ የተደረገው አገራዊ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብር፣ በሰባት ዓመታት ውስጥ 48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።

2018 .. እየተከናወነ ባለው ተጨማሪ 8 ቢሊዮን ችግኞች የመትከል ዘመቻ ደግሞ አጠቃላይ ቁጥሩን 56 ቢሊዮን በላይ በማድረስ የመሬት መልሶ ማገገም ንቅናቄውን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል።

ይህ ግዙፍ ቁጥር ከቀላል ስታቲስቲክስ በላይ የሆነ ሳይንሳዊና አህጉራዊ ትርጉም አለው። በመጀመሪያ፣ የቢሊዮን ችግኞች ስሮች አፈሩን አጥብቀው በመያዝ የላይኛው ለም አፈር እንዳይጠረግ ጠንካራ ተፈጥሮአዊ ጋሻ ይፈጥራሉ።

ሁለተኛ፣ የዝናብ ውኃ ወደ መሬት እንዲሰርግ በማድረግ የከርሰ ምድር ውኃን ያበለጽጋል፤ ምንጮች እንዲፈልቁና ወንዞች በበጋ ወቅት እንዳይደርቁ በማድረግ ድርቅን ይቋቋማል።

ሦስተኛ፣ በዛፎች ትነት አማካኝነት የአካባቢውን እርጥበት በመጨመርና ሙቀትን በመቀነስ መደበኛ የዝናብ ዑደት እንዲመለስ ያደርጋል። አራተኛ፣ የዱር እንስሳትና አእዋፍ ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ በማድረግ የስነ-ምህዳር መረጋጋትን ያረጋግጣል።

የአካባቢ ጥበቃ ሥራ አዲስ ትኩረት ማግኘቱ ያስገኘው ሌላው ትልቅ ስኬት እየተመናመኑ ያሉ የሀገር በቀል ችግኞችን ዳግም መትከል መቻሉ ነው። በዚህም የተራቆተ መሬት ምጣኔን 6 ሚሊየን ሄክታር ወደ 2.5 ሚሊየን ሄክታር ማውረድ ተችሏል።

በተጨማሪም የጎርፍ አደጋዎች እንዲሁም ድርቅና የመሬት መንሸራተት ችግሮች በከፊል እንዲቀንሱ በማድረግ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚችል ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ትርጉም ያለው ውጤት አምጥቷል።

ከስነ-ምህዳር ጥበቃ ባሻገር፣ አረንጓዴ ዐሻራው በምግብ ራስን በመቻል በኩል ፈጣን የኢኮኖሚ ትርጉም እየሰጠ ይገኛል። ማህበረሰቡ ገበያ ተኮር የሆኑ እንደ አቮካዶ እና መሰል የፍራፍሬ ምርቶችን በስፋት እንዲያመርትና ለገበያ እንዲያቀርብ በማስቻል የዜጎችን ገቢ ከፍ አድርጓል።

በተለይም በአፋር፣ በሶማሌ፣ በቦረና እና በደቡብ ኦሞ ቆላማ አካባቢዎች የተከናወነው የአረንጓዴ ዐሻራ ስራ የግጦሽ መሬቶች እንዲያገግሙና የአርብቶ አደሩ ማኅበረሰብ ኑሮ እንዲጠበቅ ስትራቴጂያዊ መሠረት ጥሏል።

በከተሞች ልማት ረገድም መርሃግብሩ ጉልህ ለውጥ እያመጣ ነው። እንደ አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት በተሰሩ የችግኝ ተከላ ስራዎች፣ አሁን በስፋት እየተከናወኑ ካሉት የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ጋር በጥብቅ የተሳሰሩ እንዲሆኑ በማድረግ፣ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ውብና ምቹ የማድረግ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል።

ይህንን ስኬት ዘላቂ ለማድረግ በአርሶ አደሮች የሚመራ የአገር በቀል ዕፅዋት መልሶ ማደግ ዘዴን መጠቀም፣ የዝናብ ውኃን ማጠራቀም፣ የነፋስ መከላከያ የዛፍ አጥሮችን መገንባትና የአካባቢውን ባህላዊ ዕውቀት በውሳኔ አሰጣጥ ውስጥ ማካተት ወሳኝ ናቸው።

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ ስራዎች እንደ ሀገር የአረንጓዴ ባህልን ከመፍጠር፣ የአየር ንብረት ለዉጥን ከመከላከል፣ የስራ ዕድልን በማስፋፋት እና የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አልፎ የሀገሪቱን የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ በማጠናከር ረገድ ትልቅ ሚና አላቸው።

ኢትዮጵያ 56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል እያስመዘገበች ያለው ተግባራዊ ስኬት፣ በረሃማነትን በመከላከልና የአየር ንብረት መዛባትን በመቋቋም ረገድ ለመላው ዓለም ተስፋ ሰጪና ፈር ቀዳጅ ተሞክሮ ሆኖ ይመዘገባል።

በበረከት ሽመልስ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: