የማዕድን ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ ውይይት እያካሄደ ነው።
ማዕድን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ምሶሶ በመሆን ምጣኔ ሀብቱ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኘ ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ በማዕድን ዘርፍ ስኬታማ ሥራዎች መሠራታቸውን እና አመርቂ አፈጻጸም መመዝገቡን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።
በኩባንያዎች እና ከባህላዊ ወርቅ አምራቾች 44 ቶን በማምረት 5.65 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ለ271 ሺ በላይ ሰዎች ከዘርፉ ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
በዘርፉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ በመስጠት እና ተኪ ምርቶችን በማምረት ረገድም ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ከወጪ ንግድ ማዕድናት 5.7 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኘ አስታውቀዋል።
ሚኒስትሩ የማዕድን ዘርፍ ከአምስቱ የሀገራችን የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ መሆኑን ገልጸው፣ ባለፉት ዓመታት የዘርፉ ዕድገት በፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን አመላክተዋል።
በቀጣይም 6.7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
በአባዲ ወይናይ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: