ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከአፍሪካ ኅብረት የጤና ዘርፍ ልዩ የመሪዎች የጤና ጉባኤ ጎን ለጎን ከጋና ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ጋር በጁብሊ ሀውስ በሁለትዮሽ እና በጋራ አህጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ከፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ መነሻ ጀምሮ ለዘለቀው ታሪካዊና ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ትልቅ ሥፍራ እንደምትሰጥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በአዲስ አበባ የሚገኘው አዲሱ የጋና ኤምባሲ ሕንፃ መጠናቀቅ የሁለቱ ሀገራት የማይናወጥ ወዳጅነት ምልክት መሆኑን በንግግራቸው አንስተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ማሃማ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነትና የአንድነት አርማነቷን እንደጠበቀች ገልጸው፣ በአሁኑ ወቅት በአረንጓዴ ዐሻራና በሌሎች የልማት ዘርፎች እያስመዘገበች ባለው አበረታች ለውጥ እና ስኬት በእጅጉ መደነቃቸውን ተናግረዋል፡፡
ሀገራችን 12ኛውን የጣና ፎረም ለማዘጋጀት እያከናወነችው ያለችው የቅድመ ዝግጅት ሥራ የሚበረታታ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ያነሱ ሲሆን፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገንም ፕሬዝዳንቱ በፎረሙ ቦርድ ላይ እያበረከቱ ላሉት የላቀ አመራር የከበረ ምስጋና አቅርበውላቸዋል፡፡
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: