Search

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የስማርት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግንባታ አስጀመሩ

ዓርብ ሐምሌ 17, 2018 121
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የስማርት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግንባታ አስጀምረዋል።
የስማርት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግንባታው ሲጠናቀቅ ወጣቶችን በማኑፋክቸሪንግ፣ በአውቶሞቲቭ፣ በኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ፣ በኮሙዩኒኬሽንስ፣ በቴክስታይል እና የሲኤንሲ (CNC) ቴክኖሎጂዎች ላይ ተግባር ላይ ያተኮረ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ሥልጠና እንደሚሰጥ ከንቲባዋ ገልጸዋል።
ሀገርን ማልማት እና ከድህነት መላቀቅ በንድፈ ሐሳብ ብቻ በተገደቡ ትምህርቶች ማሳካት ስለማይቻል፣ ሐሳብን የሚያፈልቁ አዕምሮዎችን እና የሚሠሩ እጆችን ያጣመረ ክህሎት መር የሰው ኃይል እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አመልክተዋል።
ዛሬ ያስጀመርነው ፕሮጀክት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ወጣቶቻችንን ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት፣ ከንድፈ ሐሳብ ወደ ተግባር የሚያሸጋግር፣ አዲስ የሥራ እድል የሚፈጥር የክህሎት ድልድይ የሚሆን ነው ብለዋል።
የዚህ ኮሌጅ ግንባታ በጥራትና በተቀመጠለት ጊዜ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ በልዩ ትኩረት የምንከታተለው ይሆናልም ነው ያሉት።
ፕሮጀክቱን በትብብር የሚገነባው የረጅም ጊዜ የልማት አጋር የሆነው ሰዎች ለሰዎች ድርጅት እና የሚሠራው ለትውልድ የሚሻገር ዐሻራ ነው በማለት መሬታቸውን ለፕሮጀክቱ የለቀቁ አርሶ አደሮችንም አመስግነዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: