Search

የኢቢሲ የሥራ ባልደረባ የነበሩት ወ/ሮ አልማዝ ነጋሽ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

እሑድ ሐምሌ 19, 2018 39

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሥራ ባልደረባ የነበሩት / አልማዝ ነጋሽ ሥርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት በወለቴ ለሚ ጽርሃ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

/ አልማዝ ባደረባቸው ህመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ነው በትናንትናው ዕለት 60 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

/ አልማዝ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የኦሮምኛ ፕሮግራም ክፍል የክፍሉን የዜና ቅንብር የፕሮግራም ሥራ እና በኦሮምኛ የዜና እወጃ ክፍለ ጊዜ የሚተላለፉ የጽሁፍ ሥራዎችን በመሥራት በቅንነት፣ በታማኝነትና በታታሪነት አገልግለዋል።

1986 . እስከ 2015 . 29 ዓመታት ኢቢሲን ያገለገሉት / አልማዝ ነጋሽ፣ በአገልግሎት ዘመናቸው ለተቋሙ የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት ሲያበረክቱ ቆይተዋል።

/ አልማዝ ባለትዳር እና የአንድ ሴትና የአንድ ወንድ ልጆች እናት ነበሩ።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለሥራ ባልደረቦች እና ለወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ይመኛል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: