Search

ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት ሆናለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኞ ሐምሌ 27, 2018 40

ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአንድ ጀምበር የ800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ መርሐ ግብር አፈጻጸምን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በያዘችው እቅድ መሰረት በአንድ ቀን ብቻ 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪካዊ ስኬት አስመዝግባለች ብለዋል።

በዚህም ሀገራችን ከራሷ አልፋ ለመላው አፍሪካ ታላቅ ምሳሌ መሆን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብስረዋል፡፡

በዚህ ደማቅ ሀገራዊ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ላይ 26.2 ሚሊዮን ዜጎች በነቂስ ወጥተው እጅግ ከፍተኛ እና የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸውን በመግለጫቸው አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ላሳዩት አስደናቂ ርብርብ እና ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዚሁ የአንድ ጀምበር ተሳትፎ 291.4 ሺህ ሄክታር መሬት የአረንጓዴ ዐሻራ መልበስ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

በለሚ ታደሰ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: