ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በመላው ኢትዮጵያ የተካሄደውን የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በስኬት መጠናቀቅ አስመልክተው የማጠቃለያ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም ኢትዮጵያ በተያዘላት ዕቅድ መሠረት በአንድ ቀን ብቻ 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ወደር የማይገኝለት ታሪካዊ ስኬት ማስመዝገቧን አረጋግጠዋል።
ከ26 ሚሊዮን በላይ የሚሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ዓይነት ክፍያ ሳይጠይቅ፣ አብዛኛው በዝናብ ውስጥ ሙሉ ቀን ችግኝ እየተከለ መዋሉ በዋዛ ፈዛዛ ሊተገበር የሚችል ቀላል ተግባር አለመሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጽንኦት ተናግረዋል።
ይህን ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት በከፍተኛ ጽናትና ቁርጠኝነት የተወጣውን መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከልብ ያመሰገኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ በዚሁ ልክ ተደምረን እና በአንድነት ቆመን ለነገው ትውልድ ተስፋን መትከላችን ከፍተኛ ሞራልና መነሳሳት የፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።
በዘንድሮ ዓመት እስካሁን 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ገልጸው፣ ቀሪው 1.5 ቢሊዮን ችግኞች በቀሪ ወራት የሚፈጸም ይሆናል ብለዋል።
በአድማሱ አራጋው
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: