Search

"ዛሬም በጋራ ሆነን ሌላ ታላቅ ታሪክ ፅፈናል" - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሰኞ ሐምሌ 27, 2018 26

በአዲስ አበባ ከተማተስፋን እንትከል!” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር ሲከናወን በዋለው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከዕቅድ በላይ 1.5 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ሌላ አዲስ ታሪክ መጻፉን እና አዲስ ድል መመዝገቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ ዛሬም በጋራ በመሆን ሌላ ታላቅ ታሪክ መጻፉንና ተስፋን የመትከል ስራ መከናወኑን አስታውቀዋል።

መርሐ ግብሩ እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ የከተማዋ ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣትና በሚያስደንቅ ርብርብ የተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

በእርግጥም ስንተባበር እንችላለን!” ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ሁላችንም በአንድነት ተግተን ስንሰራ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለትውልድ የሚሻገር አሻራ እና የማይነጥፍ ምንዳ እንናስቀምጣለን ብለዋል፡፡

ከንቲባዋ አክለውም፤ ይህ ታላቅ ስኬት እውን ይሆን ዘንድ ከማለዳው ጀምሮ ላደረጉት የማይታክት ጥረት፣ ላሳዩት አስደናቂ አብሮነት እና የባለቤትነት ስሜት አሻራቸውን ላኖሩ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲሁም ላስተባበሩ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: