✅ የምክክር ሂደቱ ከ10 እና ከ50 ወደ 250 ስልታዊ ቡድኖች ደረጃ የተሸጋገረ ሲሆን፣ በየቡድኑ የተመረጡ ተወካዮች የታጠሩ ሐሳቦችን በማጠናቀርና በቃለ ጉባኤ በመፈራረም ወደ 500 አባላት አጠቃላይ ጉባኤ ለማለፍ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ።
✅ ወደ 160 የሚጠጉ አመቻቾች እና ባለሙያዎች ለተመካካሪዎች ገለልተኛ እውቀትና ግብአት (በፌደራሊዝም፣ ሕገ-መንግሥት፣ ሰላም ወዘተ) የመስጠት እንጂ የራሳቸውን አቋም የመጫን መብት የላቸውም። አልፎ አልፎ የሚታዩ ግድፈቶችም በኮሚሽኑ እርምት እየተደረገባቸው ነው።
✅ ተመካካሪዎች የራሳቸው እውቀትና አቅጣጫ ያላቸው በመሆናቸው የሚጠመዘዙ አይደሉም፤ የግል/የአካባቢ ብሶቶችን ይዘው ቢመጡም ዋና ማዕከላችው ግን ኢትዮጵያ መሆኗን ይገነዘባሉ።
✅ ቃለ ጉባኤ ያዦች በከፍተኛ ፍርድ ቤቶች፣ በፍትህና በትምህርት ተቋማት የሰሩ ባለሙያዎች በመሆናቸው ውይይቱን በትክክል የመሰነድ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።
✅ በስብሰባው ላይ የሚገኙ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከንቲባዎችና ሚኒስትሮች እንደማንኛውም ተመካካሪ እኩል ተሳታፊ እንጂ ስልጣናቸውን የሚያሳዩበት መድረክ አይደለም።
✅ ምክክር ማለት መከባበርና መደማመጥ እንደመሆኑ መጠን፣ የሌሎችን ማንነት ለማሳነስ ወይም ለመጨፍለቅ የሚደረጉ ጥረቶች ትክክል እንዳልሆኑና ኮሚሽኑ በሥነ-ምግባር መመሪያው መሠረት እርምጃ እንደሚወስድ ተገልጻል።
✅ የ4000 ተመካካሪዎችን የትራንስፖርት፣ የምግብና የጤና ሁኔታ ማስተናገድ ሰፊ ስራ የሚጠይቅ ቢሆንም ሂደቱ በተቀመጠለት መርሃ ግብር መሠረት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ይገኛል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: