Search

ማንቸስተር ዩናይትድ ከፉልሃም 1 ለ 1 ተለያየ

እሑድ መስከረም 10, 2019 71
በአምስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ክራቨን ኮቴጅ ስታዲየም ተጉዞ ፉልሃምን የገጠመው ማንቸስተር ዩናይትድ 1 ለ 1 አቻ ተለያይቷል።
ማንቸስተር ዩናይትድ ከአምስቱ የሊግ ጨዋታዎች 2ኛ የአቻ ውጤት ባስመዘገበበት ጨዋታ፣ የፉልሃምን ግብ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በ63ኛው ደቂቃ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥሯል።
 
የማንቸስተር ዩናይትድን የአቻነት ግብ ደግሞ ማቲያስ ኩኛ 89ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ 5 ነጥብ የያዘው ማንቸስተር ዩናይትድ 12ኛ ደረጃን ሲይዝ፣ በውድድር ዓመቱ ለ2ኛ ጊዜ አቻ የተለያየው ፉልሃም 19ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: