Search

120 አባላት ያሉት የሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ልዑካን ቡድን ከካናዳ አዲስ አበባ ገቡ

ቅዳሜ ነሐሴ 09, 2018 47

በካናዳ የተወለዱ ሕፃናት እና ታዳጊዎች እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ያካተተ 120 አባላት ያሉት የሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ቡድኑ በኢትዮጵያ ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን፣ ስፖርታዊ ጨዋታዎችን ከታዳጊዎች ጋር እንደሚያካሂዱና የተለያዩ አካባቢዎችን እንደሚጎበኝ ይጠበቃል።

መርሐ ግብሩ ካናዳ በሚገኘው የኢፌዴሪ ኤምባሲ፣ ከቱሪዝም ሚኒስቴር እና ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ኮች አሸናፊ ግርማም አስተባባሪ በመሆን የበኩሉን ድርሻ ማበርከቱ ተገልጿል።

የሁለተኛው ትውልድ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያን የበለጠ እንዲያውቁና የባህል ትስስርን ለማጠናከር ዓላማ ያደረገው መርሐ ግብሩ፤ ለገፅታ ግንባታ፣ ለቱሪዝም፣ ለባህልና ስፖርት ዘርፍ የጎላ ፋይዳ እንዳለውም ተመላክቷል።

ቡድኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል::

በመሐመድ ራህመቶ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: