Search

“ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን ያለጦርነት መኖር አይችልም”፦ የትግራይ ወጣቶች

ማክሰኞ ነሐሴ 12, 2018 283

አፋኙ እና ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን ያለ ጦርነት መኖር የማይችል መሆኑን ከኢቲቪ ትግርኛ ጋር ቆይታ ያደረጉ የትግራይ ወጣቶች ገልጸዋል።

ይህ ኋላቀር ቡድን ለጦርነት የተፈጠረ መሆኑን የገለጹት ወጣቶቹ፣ “ቡድኑ ጦርነት ካለ ይዘርፋል፤ ተጠያቂነት አይኖርም፤ ከተጋሩ ዳያስፖራዎችም የገንዘብ መዋጮ ይጠይቃል፤ ስለዚህ ጦርነት እንዲቀጥል ይፈልጋል” ብለዋል።

ኋላቀሩ የህወሓት ቡድን ለ30 እና 40 ዓመታት የትግራይ ሕዝብ ከእሱ ሌላ እንዳያስብ ማድረጉን እና 1 ለ 5 በሚል አደረጃጀት አስሮ እንዳይቀሰቀስ ማድረጉን ተናግረዋል።

ሕዝቡ በአሁኑ ሰዓት፣ ራሱን ነጻ ለማውጣት አካታች እና ሁሉንም ያሳተፈ የመንግሥት አስተዳደር እንዲመሠረት የሚፈልግ መሆኑን ወጣቶቹ ገልጸዋል።

“የከሰረውን የህወሓት ቡድን ከሥር መሠረቱ ለማስወገድ እኛ ተጋሩ መናበብ እና ማበር አለብን፣ በተለይ ከዚህ አፋኝ ቡድን ለመላቀቅ መናበብ ያስፈልገናል፤ ሁላችንም ባለን ሙያ እና ችሎታ መታገል አለብን” ሲሉ ለመላው የትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቅርበዋል።

በጎሳዬ ገ/ኪዳን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: