በካናዳ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የአሸናፊ ግርማ ስፖርት አካዳሚ አባላት፣ ወላጆች እና አስተባባሪዎች በአዲስ አበባ የእንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞው ተጫዋች በሆነው አሸናፊ ግርማ የሚመራው ይህ የልዑካን ቡድን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች የሀገራቸውን ባህል፣ ታሪክ እና የተፈጥሮ ጸጋ በቅርበት እንዲያውቁ የሚያግዝ እና የሀገርን በጎ ገጽታ ከመገንባት ባለፈ የስፖርት ቱሪዝም ዘርፍን ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት እና አስተባባሪዎች እንዲሁም የታዳጊዎቹ ቤተሰቦች በተፈጠረላቸው የትውልድ ሀገራቸውን የመጎብኘት ዕድል መደሰታቸውን ገልጸዋል።
በተለይ በአዲስ አበባ ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ እና ፈጣን እድገት መደመማቸውን እንደተናገሩ ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: