Search

የምስራቋ ዕንቁ አዳማ በ”ሲቲ አሬና” አዲስ ገጽታዋ ተውባ አየኋት፦ የጋዜጠኛዋ ማስታወሻ

ረቡዕ ነሐሴ 13, 2018 137

ወደ አዳማ ያደረግኩት የቅርብ ጊዜ ጉዞ የቀድሞዋን ከተማ ተቀይራ አዲስና ዘመናዊ መልክ የተላበሰች አዳማን እንድመለከት አድርጎኛል።

ኢትዮጵያ በከተሞች ልማት ዘርፍ የጀመረችው የኮሪደር ልማት አገራዊ ገጽታን በመቀየርና የከተሞችን ደረጃ ወደ ላቀ ምዕራፍ በማሸጋገር ረገድ ትልቅ ስኬት እያስመዘገበ ይገኛል።

ይህ የኮሪደር ልማት የመንገድ ማሻሻያ ወይም የውጫዊ ውበት ስራ ብቻ ሳይሆን፤ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት ሳቢ፣ እንዲሁም የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት በጥራት የሚያደራጅ አዲስ የከተማ አስተዳደርና የልማት ፍልስፍና መሆኑን ተመልክቻለሁ።

በዚህ አገራዊ የትራንስፎርሜሽን ንቅናቄ ውስጥ የኢንዱስትሪ፣ የንግድና የትራንዚት ማዕከል የሆነችው አዳማ ከተማ፣ የኮሪደር ልማቱን በተግባር በመተርጎም ረገድ በምሳሌነት ከሚጠቀሱ የለውጥ አቅኚዎች አንዷ ሆና አግኝቻታለሁ።

በአዳማ ከተማ የተተገበረው ሰፊ የኮሪደር ልማት የከተማዋን መዋቅራዊ ገጽታ ሙሉ በሙሉ የቀየረ ሆኗል። ዋና ዋና የትራፊክ መስመሮችን ማስፋት፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር መንገድ ንጣፎችን ማዘጋጀት፣ የዝናብ ውሃ ማስወገጃ መስመሮችን በአዲስ መልክ መገንባትና የአረንጓዴ ስነ-ምህዳር ፓርኮችን ማስፋፋት የዚሁ ታላቅ ስራ አካል ሆነው ተገንብተዋል።

በተጨማሪም የከተማዋን ደህንነት ለማረጋገጥ የተተከሉት ዘመናዊ የጎዳና ላይ መብራቶች አዳማን በቀንም ሆነ በሌሊት ንቁ፣ ፅዱና ማራኪ አድርገዋታል፤ ይህም ለነዋሪዎች ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ከማስገኘቱም በላይ የንግድ እንቅስቃሴው ያለእረፍት እንዲቀጥል ትልቅ አቅም ፈጥሯል።

በጉዞዬ ወቅት ይበልጥ ቀልቤን የሳበውና የአዳማን የኮሪደር ልማትና የዘመናዊነት ጉዞ ወደ ላቀ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ ያሸጋገረው ደግሞአዳማ ሲቲ አሬናፕሮጀክት ተጠናቆ ለምረቃ መብቃቱ ነው።

አዳማ ሲቲ አሬና47,000 ካሬ ሜትር በላይ መሬት ላይ ያረፈ ግዙፍ ፕሮጀክት ሲሆን፤ ሁሉንም ያካተተ የገበያ ማዕከል፣ የመዝናኛ ቦታዎች፣ የስፖርት ማዕከላት፣ ሱቆች፣ የስነ-ጥበብ ኤግዚቢሽኖች፣ የሙያ ማህበራት ቢሮዎችና የምርት ማሳያዎችን በውስጡ አቅፎ ይዟል።

በአንድ ጊዜ እስከ 25,000 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን፣ 300 እስከ 400 የሚደርሱ መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማቆም የሚችል ዘመናዊ የፓርኪንግ አገልግሎትም አለው።

ይህ ፕሮጀክት ከተማዋን ወደስማርት አዳማአስተሳሰብ የሚያሸጋግር፣ የዲጂታል ኢኮኖሚን መሠረት በማድረግ ዘመናዊ፣ ፈጣንና ማራኪ ገጽታን የሚሰጥ ትልቅ ስትራቴጂካዊ እቅድ ነው።

ከዚሁ ጎን ለጎንም 3 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል። ከእነዚህም መካከል በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀና 118 ቴራባይት የመረጃ ማከማቻ አቅም ያለው የመረጃ (ዳታ) ማዕከል አንዱ ሲሆን፣ ይህም የከተማዋን የመረጃ ደህንነትና የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው።

የኮሪደር ልማቱና እንደአዳማ ሲቲ አሬናያሉ አበይት ፕሮጀክቶች አዳማን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ፣ የቱሪዝምና የዘመናዊ አገልግሎት ማዕከል በማድረግ፣ የዜጎችን ህይወት ወደ ተሻለና ወደተስፋፋ የዕድገት ደረጃ የሚያሸጋግሩ ህያው የለውጥ ምስክሮች መሆናቸውን በጉዞዬ ተመልካች ሆኛለሁ።

በኢንቲሃድ አብራር

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: