Search

‘አራዳ ሌግዠሪ ሞል’ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ በጥራት እንዲገነባ በቁርጠኝነት እንሠራለን፦ አቶ አቤ ሳኖ

ሓሙስ ነሐሴ 14, 2018 68

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የተመራው የባንኩ ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን በመሐል አዲስ አበባ እየተገነባ ያለውንአራዳ ሌግዠሪ ሞልየአፈጻጸም ሂደት በቦታው ተገኝቶ ጎብኝቷል።

ከታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ ከአራዳ ፓርክ እና ከወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር በተናበበ መልኩ የሚገነባው ዘመናዊ ሞል ለመዲናዋ ውበት የሚጨምር፣ ኢኮኖሚውን የሚያነቃቃ እና ለበርካቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር የንግድ ማዕከል ስለመሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በጉብኝቱ ወቅት፣ ባንኩ ለዚህ ፕሮጀክት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ ህንጻው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ በጥራት እንዲገነባ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ማረጋገጣቸውን የባንኩ መረጃ ያመለክታል።

115 ሺህ ካሬ ሜትር አጠቃላይ የህንፃ ስፋት ያለውአራዳ ሌግዠሪ ሞልሱፐር ማርኬቶች፣ ሲኒማ፣ ጂምናዚየም፣ ባንኮች፣ የውጭ ምንዛሬ ማዕከላት፣ ክሊኒኮች፣ ሬስቶራንቶች፣ ካፌዎች እና ሌሎች አገልግሎቶችን ያካተተ ሁለገብ የንግድ፣ የአገልግሎትና የመዝናኛ ማዕከል ሆኖ እንደሚገነባ ተገልጿል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: