Search

ከምግብ ጥገኝነት ወደ አህጉራዊ መሪነት የ'ሌማት ትሩፋት' መርሐ ግብር እና የኢትዮጵያ የግብርና ሕዳሴ ስኬቶች

ዓርብ ነሐሴ 15, 2018 119

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ለዘመናት የነበራትን እምቅ ሀብት ወደ ተጨባጭ የምግብ ዋስትና ለመቀየር የነበሩባትን ተግዳሮቶች በጽናት በመስበር ላይ ትገኛለች።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ሐሳብ አመንጪነት ጥቅምት 23 ቀን 2015 . ይፋ የተደረገው "የሌማት ትሩፋት" መርሐ ግብር ሀገራችንን ከምግብ ሸማችነት ወደ አምራችነት በማሸጋገር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተነደፈ ዐብይ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው።

ተግባራዊ የተደረጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች የግል ባለሀብቶች በፋይናንስና በቴክኖሎጂ እንዲሳተፉ በር የከፈቱ ሲሆን፣ ዘመናዊ የእንስሳት ማዳቀል፣ የሜካናይዜሽን አሰራሮች፣ የሀገር ውስጥ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ተቀናጅተው መተግበራቸው ለምርታማነት ማደግና ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

በዚህም 2014 እስከ 2018 . ባሉት አራት ዓመታት ውስጥ የወተት ማምረት አቅም 7.1 ቢሊዮን ወደ 15.7 ቢሊዮን ሊትር፣ የእንቁላል ምርት 3.2 ቢሊዮን ወደ 11.7 ቢሊዮን፣ የዶሮ ሥጋ 90 ሺህ ወደ 253 ሺህ ቶን እንዲሁም የማር ምርት ወደ 428 ሺህ ቶን ያደገ ሲሆን የዓሣ ጫጩት ስርጭት ደግሞ 300 ሺህ ወደ 16.5 ሚሊዮን አድጓል።

በተለይም 2018 በጀት ዓመት 24.2 ሺህ ቶን የእንስሳት ተዋጽኦ ለውጭ ገበያ በማቅረብ 128.4 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት የተቻለ ሲሆን፣ ይህ ስኬት የከተማ ግብርናን በማጠናከር የዜጎችን ገቢ ከመገንባቱ ባሻገር ለእናቶችና ሕፃናት የተመጣጠነ ምግብ በማቅረብ የመቀንጨር ችግርን ለመከላከል አስችሏል።

ይህንን ታሪካዊ ስኬት ዘላቂ ለማድረግ የመኖ አቅርቦትን ማዘመን፣ የሕክምና አገልግሎትን ማስፋፋትና የአምራችና ሸማቹን ቀጥታ ግንኙነት ማጠናከር የሚያስፈልግ ሲሆን፣ የሌማት ትሩፋት የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት የሚያረጋግጥ ስኬታማ ሀገራዊ መንገድ መሆኑን አረጋግጧል።

በሰለሞን ገዳ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: