የእንግሊዙ ግዙፍ ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድ የብራይተኑን ወጣት አማካኝ ካርሎስ ባሌባን በይፋ ማስፈረሙን አስታውቋል።
ካሜሩናዊው የተከላካይ አማካኝ በኦልድ ትራፎርድ እስከ ሰኔ 2031 የሚያቆየውን የ6 ዓመታት ኮንትራት የፈረመ ሲሆን፣ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ ሰኔ 2032 ድረስ ማራዘም የሚያስችል ተጨማሪ አማራጭ በውሉ ውስጥ መካተቱ ተገልጿል ።
በቀጣይ የውድድር ዘመናት የቀያይ ሰይጣኖቹ ዋነኛ አማካኝ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ባሌባ፣ በኦልድ ትራፎርድ ስኬታማ ጊዜን ለማሳለፍ እና ዋንጫዎችን ለማንሳት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
ዩናይትድ ለዚህ ዝውውር ለብራይተን 65 ሚሊዮን ፓውንድ ቀጥታ ክፍያ እና 5 ሚሊዮን ፓውንድ ተጨማሪ የሚከፍል ሲሆን፣ ብራይተን ወደፊት ተጫዋቹ ከሚሸጥበት ዋጋ ድርሻ የሚያገኝበትን ስምምነትም መካተቱ ተዘግቧል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: