Search

በከተማችን ላይ ከሚታየው ለውጥ ሁሉ የሚልቀው በለነገዋ ሴቶች ላይ እያየን ያለው ለውጥ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ማክሰኞ ነሐሴ 19, 2018 44

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት የልጆች ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) መስራች እና የቦርድ ኃላፊ ክሪስ ሆን እና ቡድናቸውን ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ማስጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

ከንቲባዋ ለነገዋ ጅማሮው በተለያዩ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ያሉ ሴቶች እህቶቻችን ተስፋና እድላቸው እንዲለመልም፣ ክብራቸውና ደኅንነታቸው ተጠብቆ የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ ከልብ በመነጨ ስሜት የተፀነሰ፣ ተፀንሶም ወደ ተግባር የተቀየረ ትልቅ ራዕይን የሰነቀ ሥራ መሆኑን ገልጸዋል።

የእነዚህ እህቶቻችንን ህይወት ለመቀየር፣ ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል 2016 . ጀምረነው 5 ዙር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች 3 ሺህ 259 ሰልጣኞችን በክህሎት እና በስብዕና ግንባታ አሰልጥነን ወደ ሥራ አሰማርተናል ነው ያሉት።

ዛሬ ሁሉም ተመራቂዎች ክብር ያለው ኑሮ፣ ብሩህ ተስፋን ሰንቀው አዲስ ህይወት መኖር መጀመራቸውንም ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ከምንሰራቸው ሥራዎች ሁሉ ትልቁ ሥራ በሰው ላይ የምንሰራው፣ በተለይም በሴቶች ላይ የምንሰራው ነውየሚለውን የጠቅላይ ሚኒስትራችን ዐቢይ አሕመድ (/) መልዕክት የሥራችን ማዕከል አድርገን እየፈፀምን እንገኛለን ብለዋል።

በከተማችን ላይ ከሚታየው ለውጥ ሁሉ የሚልቀው በለነገዋ ሴቶች ላይ እያየን ያለው ለውጥ ነው ያሉት ከንቲባዋ፣ ለነገዋ የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከልየሰነቅነው ራዕይ፣ በዓመት እስከ 10 ሺህ ሴቶችን የሚያበቃ  እንዲሁም አካታች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ልምድ የሚቀሰምበት የልህቀት ማዕከል እንዲሆን ማስቻል ነው ሲሉም አመልክተዋል።

ይህ ራዕይ በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ሊደግፋን የመጡት የልጆች ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) መስራች ክሪስን በለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የምንሰራቸው ሰው ተኮር ስራዎች አስጎብኝተን በቀጣይም በጋራ በምንሰራቸው ሥራዎች ዙሪያ ተወያይተናል ብለዋል።

ለራዕያችን ግብ ስኬት ሌት ተቀን ተግተን እንሰራለን፤ ፈጣሪም ይረዳናል ሲሉም አረጋግጠዋል

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: