ኢትዮጵያ በአካባቢ እና በሰው ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ "የማይመክኑ ኦርጋኒክ በካዮችን" ለመቆጣጠር እና ለማስወገድ የገባችውን ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን በተግባር ለመተርጎም እየሰራች መሆኗ ተገለጸ።
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የስቶክሆልም የማይመክኑ ኦርጋኒክ በካዮች ዓለም አቀፍ ስምምነትን ለማስፈጸም የሚያግዝ "የተሻሻለ ብሔራዊ የትግበራ ዕቅድ" ላይ የሚመክር ወርክሾፕ በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
የስቶክሆልም ስምምነት በአካባቢ ላይ ረጅም ጊዜ የሚቆዩ፣ በሰውና በእንስሳት አካል ውስጥ የሚከማቹ፣ ረጅም ርቀት በመጓዝ በጤና ላይ ከፍተኛ አደጋ የሚጋርጡ ቀጣይነት ያላቸው ብክለቶችን ለመቀነስና ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስምምነት ነው።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የስምምነቱ ፈራሚ እንደመሆኗ መጠን ግዴታዋን ለመወጣት በርካታ ሥራዎችን እያከናወነች ትገኛለች።
በስምምነቱ የተካተቱ አደገኛ ቁሳቁስን በአካባቢና በጤና ላይ ጉዳት በማያስከትል መንገድ ማስወገድ፣ የተቋማትንና የባለሙያዎችን አቅም ማጠናከር፣ የህግና የቁጥጥር ማዕቀፎችን በዘመናዊ መንገድ መቅረጽ ዋነኞቹ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው።
በስምምነቱ የተያዙ ቁሳቁስ በአካባቢና በጤና ላይ ጉዳት በማያስከትል መንገድ ማስወገድ፣ የተቋማትና የባለሙያዎችን አቅም ማጠናከር እንደሁም የህግና ቁጥጥር ማዕቀፎችን ማጠናከር ላይ እየተሠራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።
እየተካሄደ ያለው ወርክሾፕ፣ ብሔራዊ የትግበራ ዕቅዱ የመጨረሻ ቅርጽ ከመያዙ በፊት ክፍተቶችን ለመለየትና ሰነዱን ይበልጥ ለማዳበር የሚያግዝ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የአካባቢ ደኅንነትን ለመጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንደሆነም በዚህ ወቅት ተነስቷል።
በዓባዲ ወይናይ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: