በትምህርት ዘመኑ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ 563 ሺህ 501 ተማሪዎች መካከል 70 ሺህ 544 የሚሆኑት ማለፋቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፈተናውን ውጤት አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ በማምጣት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚቀላቀሉት ተማሪዎች 12.8 በመቶ ሲሆኑ፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር አበረታች ለውጥ የታየበት መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም ባለፈው ዓመት ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ቁጥር 62 የነበረ ሲሆን፣ በዘንድሮው ዓመት ይህ ቁጥር ወደ 88 ከፍ ማለቱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በተቃራኒው ደግሞ ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ባለፈው ዓመት ከነበረው 1 ሺህ 230 ዘንድሮ ወደ 565 ዝቅ ማለቱ በትምህርት ዘርፉ የታየው መሻሻል ማሳያ መሆኑ ተጠቁሟል።
በኤዶምያስ ንጉሤ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: