Search

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቸሰተር ዩናይትድ በሃል ሲቲ 2 ለ 0 ተሸነፈ

ቅዳሜ ነሐሴ 16, 2018 96

ትላንት በተጀመረው 2026/27 የውድድር ዘመን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኤምኬኤም ስታዲየም አዲስ አዳጊውን ሃል ሲቲን የገጠመው ማንቸስተር ዩናይትድ 2 0 ተሸንፏል።

አዳዲሶቹ ፈራሚዎች ዮሪ ቴሌማንስና አንድሬ ሳንቶስ ቋሚ ተሰላፊ ሆነው በጀመሩበት እንዲሁም ማርከስ ራሽፎርድ ተቀይሮ በገባበት ጨዋታ፤ ሃል ሲቲ የማሸነፊያዎቹን ሁለት ግቦች በመጀመሪያው አጋማሽ ነው ያስቆጠረው።

17ኛው ደቂቃ ላይ ሰሚ አጃዬ እንዲሁም ኖቤል ሜንዲ 38ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠሯቸው ግቦች ሃል ሲቲ የውድድር ዓመቱን በድል እንዲጀምር አስችለዋል።

በታሪኩ በፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዩናይትድን አሸንፎ ለማያውቀው ሃል ሲቲ ይህ ድል የመጀመሪያ ሆኖ ተመዝግቦለታል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: