የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተመዘገቡ ከፍተኛ ውጤቶችን ይፋ አድርገዋል።
በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ በወንዶች ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በአዳማ ኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ሲሆን፣ 591.6 ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ቀዳሚ ሆኗል።
በተመሳሳይ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ በሴቶች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው ተማሪ እንጅባራ ከሚገኘው አገው ምድር ትምህርት ቤት ስትሆን፣ 583 አምጥታለች።
በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በወንዶች የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 576.25 ሲሆን፣ ትምህርት ቤቱም ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት እንደሆነ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በዚሁ ዘርፍ በሴቶች ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በአዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው ሱፐር ሆሊ ሴቪየር ትምህርት ቤት ሲሆን፣ የተማሪዋ ውጤትም 569.1 ሆኖ መመዝገቡን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል።
በሐና ምንዳሁን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: