Search

1501ኛው መውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ እየተከበረ ነው

ማክሰኞ ነሐሴ 19, 2018 46

1501ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰዐወ) መውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ በድምቀት እየከበረ ይገኛል።

ሕዝበ ሙስሊሙ የታላቁን ነቢይ ሙሐመድ (ሰዐወ) የልደት በዓል የነቢዩን አስተምህሮ እና የህይወት ፈለግ በመከተል አቅመ ደካሞችን በመደገፍና በማገዝ ማክበር እንደሚገባ ተገልጿል።.

በታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሰዐወ) ላይ የወረደው መለኮታዊ መመሪያ የሆነው ቁርዓን፣ በተግባር  የህይወት ፈለጋቸውን እና አስተምሯቸውን ለመላው የሰው ልጅ መሪ ብርሃን ሆኖ የሚያገለግል ነው።

ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር ለአቅመ ደካሞች እና ከቀዬያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ በማጠናከር እንዲሁም ለሀገር ሰላም እና ለሕዝቦች አንድነት ዱዓ በማድረግ እንዲያከብር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት ጥሪ አቅርቧል።

በላሉ ኢታላ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: