Search

ዜጎች ሥራ ፈጣሪ፣ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አመርቂ ሥራዎች ተሠርቷል፡- የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

ሰኞ ነሐሴ 25, 2018 157

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባለፉት አምስት ዓመታት ባስመዘገባቸው ውጤቶች እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይትና የሥራ ፈጠራን የሚያሳይ ክህሎት ኢትዮጵያ ዐውደ ርዕይ በኢዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ተጀምሯል።

የሥራ ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል  በንግግራቸው ተቋሙ  ባለፉት አምስት ዓመታት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡንና ዜጎች ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሆኑና ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ በርካታ ሥራዎች ማከናወኑን ገልጸዋል።

ዜጎች ወቅቱ በሚጠይቀው ዲጂታል ዘርፍ ጭምር ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በዲጂታል ሙያ ዘርፎችም እንዲሳተፉ መደረጉን ጠቁመዋል።

መድረኩ በሥራ ዕድል፣ በክህሎት ልማት እንዲሁም በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ የተመዘገቡ ዋና ዋና የልማት ስኬቶችን፣ ልምዶችንና የወደፊት አቅጣጫዎችን ለማመላከት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ለአራት ቀናት በሚቆየው በሥራ ፈጣሪዎች ኤግዚቪሽን የተሳተፉ ወጣቶች የሥራ ፈጠራ ክህሎታቸውን እያዳበሩና የተለያየ ሙያ ባለቤት በመሆናቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባለፉት አምስት አመታት በርካታ ወጣቶች  ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩና ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ እድሎችን ማመቻቸቱም ተጠቁሟል።

በዐውደ ርዕይዩ የቀረቡ የፈጠራ ሥራዎችን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጎብኝተውታል።

 

በመሃሪ አለሙ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: