Search

የኢትዮጵያ የገቢና ወጪ ንግድን ያቀላጠፈ የሁለቱ ተቋማት ጠንካራ አጋርነት

ሰኞ ነሐሴ 25, 2018 120
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ከኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ ጋር ያለውን የጋራ ስኬትና ጠንካራ አጋርነት የሚገመግም ልዩ መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
እነዚህ ሁለት ግዙፍ ተቋማት የኢትዮጵያን የገቢና ወጪ ንግድ በላቀ ቅልጥፍና በማከናወን ረገድ የጀርባ አጥንት ሆነው እያገለገሉ እንደሚገኙ በመድረኩ ላይ ተመላክቷል።
በተለይም ኢትዮጵያ የጀመረችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውጤታማ ለማድረግ፣ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን መቋቋም የሚችልና ዘመናዊ የሎጀስቲክስ ሰንሰለት በመዘርጋት ረገድ የጋራ ጥረታቸው ስኬታማ መሆኑ ተገልጿል።
ተቋማቱ የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ውጤት መሸከም የሚችል የሎጀስቲክስ ሰንስለት መዘርጋታቸው ውጤታማ እንዳደረጋቸውም አስታውቀዋል፡፡
አሁንም የሎጅስቲክስ ወጪን በመቀነስና የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ስራ በመስራት ኢንቨስትመንትን መሳብ እንደሚገባ በመድረኩ ተመላክቷል።
በአዝመራው ሞሴ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: